Dilla University

Articles

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ መምህራን ተግተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ

22069062 1623502591040566 909427986 o

ዲላ፣ መስከረም፣8፣ 2010 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግንኙነት) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች የስልጠናና የምክክር መድረክ በትምህርት ጥራት ጉዳይ፣ በስኬታማ አሰራር ሥርዓት (Deliverology)፣ በሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት ውጤታማነት እና የዩኒቨርሲቲውን የ2010 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ውይይት ተካሄደ።

ሰኞ መስከረም 8 ቀን 2010 ዓ.ም “መምህርነት ቅድመ ሁኔታ የማይገድበው ባላደራነት” በሚል ርዕስ በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው ከመድረክ በተሰጠው ገለፃ የተጀመረው የመምህራን ስልጠናና ውይይት መድረክ የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ መሰረት ባደረጉ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ ለተከታታይ አምስት ቀናት ተካሂዷል።

በዋናው መድረክ የተሰጠውን ገለፃ ተከትሎ መምህራን በየኮሌጃቸው ውይይት ያደረጉ ሲሆን ለትምህርት ጥራት ጉድለቶች ምክንያት ያሏቸውን ጉዳዮች ዘርዝረዋል። የመምህራን የማስተማር ብቃት መጓደል፣ መምህራን የሴሚስተሩን የትምህርት ጊዜ በሁለት ቀን መጨረስ፣ የተማሪዎች ቅበላ ቁጥር ከዩኒቨርሲቲው አቅም በላይ መሆንና ለከፍተኛ ትምህርት ብቁ ያልሆኑ ተማሪዎች መመደብ ለትምህርት ጥራት እንደችግር በመድረኩ ላይ ከተነሱ ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል።

ከመምህራን በተነሱ ሀሳቦች ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ቃልኪዳን ነጋሽ የዩኒቨርሲቲውን እቅድና አላማ ለመምህራኑ ያስረዱ ሲሆን የመምህራን ክፍል ገብቶ የማስተማር ችግርን አስመልከቶ ሲናገሩ በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ክፍል ገብቶ ማስተማር ትንሹ ከመምህራን የሚጠበቅ ግዴታ መሆኑን አበክረው ተናግረዋል። እንዲሁም ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሰጥ የሚያስችሉ ተግባራት እንደሚከናወኑና የቁጥጥር ስራ በቀጣይ በተጠናከረ መንገድ ይሰራል ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከተማሪዎች አቅም ማነስ በበለጠ የመምህራን የማስተማር ብቃት ትኩረት ሊሰጠው እንሚገባ በመድረኩ ላይ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ለዚህም በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አሁን በማስተማር ላይ ላሉ መምህራን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ተዘጋጅቶ ለመስጠትና የመለየት ስራ ለመስራት እቅድ እንዳለ አስረድተዋል። በመሆኑም መምህራን ዘመኑ በፈጠረው ቴክኖሎጂ እራስን ከማብቃቱ ተግባር ጎን ለጎብ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ግንባር ቀደም ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመምህራን ከተነሱ ጉዳዮች አንዱ የመምህራን እድገት አሰጣጥ ይገኝበታል። በዩኒቨርሲቲው ያለው የመምህራን ደረጃ እድገት አሰጣጥን አስመልክቶም በዩኒቨርሲቲው ቀደም ሲል አገልጎለት ላይ ይውል የነበረው መመሪያ ከደረጃ በታች መሆኑና አዳኝ ጆርናሎች (predatory journal) ከመብዛታቸው ጋር በተያያዘ መመሪያውን ማሻሻል በማስፈለጉ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መገባቱንና በቅርብ ጊዜ ውስጥ አዲሱ መመሪያ ጸድቆ ስራ ላይ እንደሚውል ታውቋል።        

በዚሁ የውይይትና ስልጠና መድረክ የውጤታማነት ስኬት አሰራር ሥርዓት (Deliverology) ፅንሰ ሀሳብ በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ አስፈላጊነትና የማስፈፀሚያ ስልቶቹ ዙሪያ ውይይት ተደርጎል። የውጤታማነት ትግበራ (Deliverology) የዩኒቨርሲቲውን ስራ ሳይንሳዊ ከማድረግ አኳያና የተማሪዎችን የመቀጠር ምጣኔ በተመረቁ በአስራ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ 80 ከመቶ ከማድረስ አኳያ ወደትግበራ አግባብነት እንዳለው በውይይቱ መግባባት ለይ ተደርሷል። የውጤታማነት ትግበራ ጋር ተያይዞ የተማሪዎችንና የመምህራንን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለማሻሻል የኤ.ሊ.ክ ማህከልን አጠናክሮ ስልጠና መስጠት እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ተነግሯል።

የሥነ-ምግባርና የሥነ-ዜጋ ትምህርትን አስመልክቶ መምህራን ባደረጉት ውይይት መብቱን የሚጠይቅ ወጣት መፍጠር ቢቻልም ግዴታውን ከመወጣት አኳያ ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩና ተማሪዎችና መምህራን በአለባበስና ነፀጉር አቆራረጥ ሥነ-ምግባርን ከመጠበቅ አኳያ ችግሮች እንደሚስተዋሉ ተጠቅሰዋል። በዩኒቨርሲቲው ዙሪያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየተስፋፋ የመጣው የጫትና የሺሻ ማስጨሻ ቤቶች ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሆኖ ስራ መስራትና ማዘጋት እንደሚገባም መግባባት ላይ ተደርሷል። የፆታ ትንኮሳ ጉዳይም ትኩረት ያስፈልገዋል በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው የህግ መመሪያ አዘጋጅቶ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ያቀርባል ተብሏል።

አጠቃላይ የስልጠናና ውይይት መድረኩን አስመልክቶ ከዚህ በፊት ይታዩ የነበሩ የውይይት አጀንዳዎች ከመማር ማስተማር ጋር የማይገናኙ ከመሆናቸው ጋር በተያያዘ መምህራን ደስተኛ አንዳልነበሩና በዚህ ዘመት ግን ጉዳዩ ይበልጥ ከስራቸው ጋር የሚገናኝ መሆኑ እንዳስደሰታቸውና ተገቢ የውይይት አጀንዳ እንደነበር ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ለአስተዳደር ሰራተኞች ኦዳ ያኣ ጊቢ በሰራተኞች ሥነ-ምግባርና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ነው። በአስተዳደር ሰራተኞች መድረክም ሰራተኞች እራሳቸው በመገምገም ተገልጋይን በአግባቡ ያለማስተናገድ፣ ከስራ ሰዓት ዘግይቶ መግባትና ቀድሞ መውጣት እንዲሁም ከፍተኛ የሥነ-ምግባር ችግሮች እንደሚስተዋሉ በመድረኩ ተነግሯል። በቀጣይ የየክፍሉ የስራ ኃላፊዎች በስራቸው ያሉ ሰራተኞችን ሊቆጣጠሩ እንደሚገባና ከመስመር የወጡ ሰራተኞች ላይም ተመጣጣኝ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ ተነግሯል።

በመጨረሻው ቀን የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት በተገኙበት መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ተወያይተው የደረሱባቸውን ጉዳዮች ተለይተው ተጨማሪ ማብራሪያ የሚጠይቁ ጉዳዮች ካሉ መምህራን እንዲናገሩ እድሉ ተሰጥቶ የነበረ ሲሆን መምህራኑ የቦርድ አባላቱ የዩኒቨርሲቲው ችግሮች ከመፍታት አኳያ የድጋፍና ክትትል ስራ አጠናክረው እንዲሰሩ ጠይቀዋል። የንጹ መጠጥ ውሃ፣ የመኖሪያ ቤት፣ የተማሪዎችና የመምህራን መዝናኛ ቦታዎች ችግር፣በዩኒቨርሲቲው በእኩል የተጠያቂነት አሰራር እንዲጎለብት እና የመምህራን የትምህርት እድል ችግሮች አስመልክቶ ችግሮች ተነስተዋል።

ከዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት መካከል የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳደር የሆኑት አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ ተቋሙ የቦርዱን የቅርብ ክትትል እንደሚያስፈልገውና የጠባብነትን ችግር በመፍታት ተግባር፣ ኪራይ ሰብሳቢነትን በተመለከተ ከስሩ አጥርቶ ለመቅረፍ፣ እና ዩኒቨርሲቲውን በተማሪዎች ተወዳጅ ተመራጭ ለማድረግ ከመምህራን ጎን ሆነው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

***

şişli escort istanbul escort antalya escort beylikdz escort ankara escort halkali escort ataköy escort şirinevler escort beylikdz escort istanbul escort istanbul escort pendik escort hacklink hacklink al hacklink satin al