Dilla University

Articles

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከተቋቋመ በታሪኩ ከፍተኛዉን የተማሪ ቁጥር አስመረቀ

5B9A3162 A

በሙሉቀን አሰግደው

በ1989 ዓ/ም ዲላ ጤና ሳይነስና መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በሚል ከተቋቋመ ዛሬ 20 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በ20 ዓመታት ጉዙዉ ዉስጥ ከኮሌጅነት በ1999 ወደ ዩኒቨርሲቲነት አድጓል፡፡ አሁን 55 የመጀመሪያ ድግሪ እና 41 የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን በመክፈት አስከ 30 ሺ የሚደርሱ ተማሪዎችን በተለያዩ መረሀ ግብሮች የማስተናገድ አቅም ፈጥሯል፡፡

የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ቃልኪዳን ነጋሽ ዩኒቨርሲቲዉ በዚህ ዓመት ከተመሰረት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉን ተማሪዎች ማስመረቅ መቻሉ ከ20ኛው ዓመት ምስረታ በዓሉ ዋዜማ ጋር መገጣጠሙ የዚህን ምረቃ በዓል ልዩ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በመክፈቻ ንግግራቸዉ በ2010 መግቢያ የ20ኛ ዓመት ምስረታ ቀኑን ስናከብር ‹‹ ዩኒቨርሲቲዉ በሃያ ዓመታት ቆይታዉ ያስመዘገባቸዉን ዉጤቶችንም ሆነ የገጠሙትን ፈተናዎች ቆም ብሎ ለማጤን ብሎም የተቋሙን የወደፊት ራዕይ እና ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ልዩ አጋጣሚ ይፈጥራል ›› ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ ዩኒቨርሲቲዉ የመጀመሪያ ደረጃ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ ከዚሁ ደረጃው ጋር የሚመጣጠን የማስፋፊያ እና መሰረተ ልማት ማሟላት እንደሚያስፈልግ አጸንወት ሰጥተዉበታል፡፡ ከዚህም በላይ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች አንፃር የልህቀት ማዕከል የሚሆንበትን የትምህርትና ምርምር መስክ ለይቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲዉን እንቅስቃሴ በኢንፎርሜሽን እና ኮሚኒኬሽን ለመደገፍ እና ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር ለማስተሳሰር የማህበረሰብ ሬድዮ ለማቋቋም በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ሌላው የትምህረት ጥራትን ማሻሻል ልዩ ትኩረት የሚያሻ ጉዳይ ሲሆን የመምህራን ልማት ላይ የተቀመጠዉን (0፡70፡30) ማለትም በመጀመሪያ ድግሪ የሚያስተምር መምህር 0 በመቶ፣ ሁለተኛ ድግሪ ያላቸው መመህርን 70 በመቶ እንዲሁም 30 በመቶው ደግሞ ሦሥተኛ ድግሪ ያላቸው መምህራን እንዲሆኑ በ2012 ዓ/ም ለማሳካት እየተሰራዉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ መለሰ አለሙ የደ/ህ/ብ/ብ/ክ/መ/ም/ ርዕሰ መስተዳደር፣የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ስራ አመራር ቦርድ ሰበሳቢ ተመራቂዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸዉ ያካበቱትን እዉቀትና ክህሎት በመጠቀም ህዝብ እና ሃገር በታማኝነት እንዲያገለግሉ አሳስበዋል፡፡

የክብር ዕንግዳው የድህነት እና የዴሚክራሲ ችግር የሚፈታዉ በእዉቀት እና ትምህርት በመሆኑ መንግስት ለትምህርት እና ሥልጠናዉ ዘርፍ ትኩረት መስጠቱን ጠቁመዋል፡፡ የተማረ ማህበረሰብ በምክንያት የሚደግፍ እና የሚተች በመሆኑ ተመራቂዎች ከስሜት በጸዳ መልኩ በመልካም አስተዳደር፣ ዲሞክራሲ እና ሃገር ግንባታ በንቃት እንዲረባረቡ ጠይቀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዉ በህክምና ሳይንስ (Doctor of medicine (MD) ፣ በሥነ ተዋልዶ እና እንዲሁም በኮንፒዉተር እና ኔትወርኪንግ ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ አሥመርቋል፡፡

በምረቃዉ ሥነ-ሥርዓት ከእየኮሌጁ ከፍተኛ ዉጤት ያመጡ ተመራቂዎች ከእለቱ የክብረ እንገዳ እጅ የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት ወስደዋል፡፡

ከ2009 ዓ/ም አጠቃላይ ተመራቂዎች ከፍተኛ ዉጤት ያስመዘገቡት ተማሪ ሃብታሙ አባይነው ከአግሮ ኢኮኖሚ ትምህረት ክፍል እና ከሴት ተመራቂ ተማሪዎች ከፋተኛ ውጤት ያስመዘገበችው ተማሪ ረዴት ጊዳ ከሚድ-ዋይፊሪ ትምህርት ክፍል የዋንጫ ሽልማታቸዉን ከዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት እጅ ተቀብለዋል፡፡

şişli escort istanbul escort antalya escort beylikdz escort ankara escort halkali escort ataköy escort şirinevler escort beylikdz escort istanbul escort istanbul escort pendik escort hacklink hacklink al hacklink satin al