Dilla University

Articles

6ኛ ዙር ሀገር አቀፍ ምርምር ዉይይት የትምህርት ጥራት ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ቃል ተካሄደ፡፡

5B9A1686

በአማኑኤል ብርሃኑ

ዉይይትን በንግግር የከፈቱት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ተወካይና ዶ/ር ተሾመ ጉዲሳ ዩኒቨርሲቲዉ እከናወናቸዉ ያሉትን የምርምር ሥራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በጥራት እያበራከቱ መሆናቸዉን በመግለፅ በትምህርት ጥራት ላይ የምሰሩ የጥናትና ምርምር ዉጤቶች እስከ ታችኞቹ መዋቀር ወርደዉ ችግሩን በዘላቂነት መፍታት እንደሚችሉ የሚቀረቡት የምርምር ሥራዎች መምህራን ሰፊ ተሞክሮዎችን የሚለዋወጡበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የትምህርት ስነ ባህሪ እንሲቱት ዲን ዶ/ር ደረጀ ደምሴ በበኩላቸዉ ዘንድሮ በተዘጋጀዉ ዉይይት ላይ ከመቶ የሚበልጡ ተመራማሪዎች ግኝቶቻቸዉን ለማቅረብ እንዳመለከቱ በመግለፅ ከነዚህ ዉስጥ አስራ ስድስት የምርምር ፁሁፎች በሀገሪቱ ካሉት ዩኒቨርሲቲዎች በተወጣጡ ተመራማሪዎች ቀርበዉ የማህበረሰቡንና የትምህርት ቤቶቻቸዉን ችግሮች በመፍታት የትምህርትን ጥራት ሊያረጋግጥ እንደሚችል አስገልዝበዋል፡፡

በዉይይት ላይ የተገኙ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር የአካዳሚክና የምርምር ጉዳዮች ጄኔራል ዳይሬክተር እንዲሁም የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ አባል ዶ/ር ሹመቴ ግዛዉ በሀገሪቱ የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ችግሮቹን በተጨማሪም መልኩ መፍታት የምችሉ እንደሆነ በመግለፅ የምርምር ዉጤት ለማንኘዉም ማህበረሰብ ሊጠቅም በሚችል መልኩ ቴክኖሎጂዉን ሊያሻግር በሚችል መልኩ ምርምሮች መሰራት አለበት ካሉ በኃላ የጥራት ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉም በያለበት የድርሻዉን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡

በመጨረሻም የስነ ባህሪ ኢንስቲቱት ዲን ዶ/ር ደረጄ ደምሴ እና ም/ዲን ዶ/ር ደጀኔ ተፈራ ለዉይይቱ መሳከላት ለት ተቀን ደከመን ሰለቸን ሳይሉ ያገለገሉትን ዉይይትን አዘጋጅ ኮሚቴዎችን በዲፓርትመንታቸዉና በራሳቸዉ ስም በማመስገን ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለተወጣጡ ተመራማሪዎች እና ለኮሜቴዎቹ የምስጋና ወረቀት አበርክተዋል፡፡

ዉይይቱ ላይተሳትፈዉ ጽሁፋቸዉን ያቀረቡ ተመራማሪዎችም እነሱ ካቀረቡት ጽሁፍ ባለፈ ሌሎች ባቀረቡት ጽሁፍ ትምህርት ማግኘታቸዉን ተናግረዋል፡፡

5B9A1706

şişli escort istanbul escort antalya escort beylikdz escort ankara escort halkali escort ataköy escort şirinevler escort beylikdz escort istanbul escort istanbul escort pendik escort hacklink hacklink al hacklink satin al